Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሐዋርያት ሥራ 4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ንስ በካ​ህ​ናት ሸንጎ ፊት

1 ሕዝ​ቡ​ንም ሲያ​ስ​ተ​ምሩ ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደስ ሹም፥ ሰዱ​ቃ​ው​ያ​ንም መጡ።

2 ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ።

3 እጃ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው ያዙ​አ​ቸው፤ ጊዜ​ዉም ፈጽሞ መሽቶ ነበ​ርና እስከ ማግ​ሥቱ ድረስ በወ​ኅኒ ቤት አገ​ቡ​አ​ቸው።

4 ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ።

5 በማ​ግ​ሥ​ቱም አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውና ሽማ​ግ​ሎች፥ ጻፎ​ችም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።

6 ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።

7 በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።

8 ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤

9 ዛሬ ለበ​ሽ​ተ​ኛው በተ​ደ​ረ​ገው ረድ​ኤት ምክ​ን​ያት በእ​ና​ንተ ዘንድ እኛ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ብን ከሆነ እን​ግ​ዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ?

10 እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።

11 ይህ እና​ንተ ግን​በ​ኞች የና​ቃ​ች​ሁት ድን​ጋይ ነውና፤ እር​ሱም የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነ።

12 መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”

13 ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።

14 ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ።

15 ከሸ​ን​ጎ​ውም ጥቂት ፈቀቅ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸ​ውና እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ።

16 እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚ​ህን ሰዎች ምን እና​ድ​ር​ጋ​ቸው? እነሆ፥ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ደ​ረ​ገው ተአ​ምር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግል​ጥም ሆነ፤ ልን​ሰ​ው​ረ​ውም አን​ች​ልም።

17 ነገር ግን በሕ​ዝቡ ዘንድ እጅግ እን​ዳ​ይ​ስ​ፋፋ ዳግ​መኛ በኢ​የ​ሱስ ስም ሰውን እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ አጠ​ን​ክ​ረን እን​ገ​ሥ​ጻ​ቸው።”

18 ጠር​ተ​ውም፦“ በኢ​የ​ሱስ ስም ፈጽሞ አት​ና​ገሩ አታ​ስ​ተ​ም​ሩም” ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው።

19 ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።

20 እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።”

21 እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።

22 ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።

23 ተፈ​ት​ተ​ውም ወደ ሰዎ​ቻ​ቸው ሄዱ፤ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያሉ​አ​ቸ​ውን ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።

24 ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት ቃላ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ አድ​ር​ገው እን​ዲህ አሉ፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠ​ርህ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥

25 አንተ ራስህ በአ​ባ​ታ​ችን በባ​ሪ​ያህ በዳ​ዊት አፍ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብለህ የተ​ና​ገ​ርህ፦ አሕ​ዛብ ለምን ተሰ​በ​ሰቡ? ሕዝ​ቡስ ለምን ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ?

26 የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ለምን ተነሡ? አለ​ቆ​ችስ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ረው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ ለምን ዶለቱ?

27 በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።

28 እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ።

29 አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው።

30 በቅ​ዱሱ ልጅ​ህም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሕሙ​ማ​ንን ትፈ​ውስ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራ​ንም ታደ​ርግ ዘንድ እጅ​ህን ዘርጋ።”

31 ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ።


ስለ ምእ​መ​ናን አን​ድ​ነት

32 ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።

33 ሐዋ​ር​ያ​ትም የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ትን​ሣኤ በታ​ላቅ ኀይል ይመ​ሰ​ክሩ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ዘንድ ታላቅ ጸጋ ነበ​ራ​ቸው።

34 ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር።

35 አም​ጥ​ተ​ውም በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ፍላ​ጎቱ ይከ​ፍ​ሉት ነበር።

36 በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ዘንድ ትር​ጓ​ሜዉ የመ​ጽ​ና​ናት ልጅ የሚ​ሆን በር​ና​ባስ የተ​ባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚ​ሉት አንድ የቆ​ጵ​ሮስ ሰው ነበር።

37 እር​ሻም ነበ​ረ​ውና ሽጦ ገን​ዘ​ቡን አም​ጥቶ በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ አኖ​ረው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች