የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ማቴዎስ 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡም በመቈጣት ሰራዊቱን ልኮ ገዳዮቻቸውን አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡም ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ተቍኦጣ፥ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ማቴዎስ 22:7
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው፤ ገደሉአቸውም።


በዚያን ጊዜ ባሮቹን ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤


ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


ያን​ጊዜ በይ​ሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያሉም ከእ​ር​ስዋ ይውጡ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ያሉም ወደ እር​ስዋ አይ​ግቡ።


በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።