Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ያን​ጊዜ በይ​ሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያሉም ከእ​ር​ስዋ ይውጡ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ያሉም ወደ እር​ስዋ አይ​ግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚያ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በከተማ ያሉትም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉትም ወደ ከተማዪቱ አይግቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፤ በመካከልዋም ያሉ ከእርሷ ይራቁ፤ በገጠር ያሉም ወደ እርሷ አይግቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፤ በከተማይቱ ውስጥ ያሉ ከዚያ ይውጡ፤ ከከተማ ውጪ ያሉትም ወደ ከተማይቱ አይግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:21
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”


የሎ​ጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ የጨው ሐው​ል​ትም ሆነች።


ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዚች ምድር ላይ በዘ​መተ ጊዜ፦ ኑ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትና ከሶ​ርያ ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሂድ፤ አልን፤ እን​ዲ​ሁም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መ​ጥን።”


ኤር​ም​ያስ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ይኖር ዘንድ ወደ ብን​ያም ሀገር ሊሄድ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


ማኅ​በ​ሩ​ንም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ክፉ​ዎች ሰዎች ድን​ኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ት​ጠፉ ለእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አት​ንኩ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥


በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ፤ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፤


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች