Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ ኢየሩሳሌምም የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉ ይሰደዳሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:24
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ም​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እኅ​ታ​ቸው ዲና​ንም ከሴ​ኬም ቤት ይዘው ወጡ።


ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።


አሁ​ንም በወ​ይኔ ላይ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አጥ​ሩን እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤ ለብ​ዝ​በ​ዛም ይሆ​ናል፤ ቅጥ​ሩ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ለመ​ራ​ገ​ጫም ይሆ​ናል።


በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራህ ከር​ስ​ትህ ጥቂት ክፍል እና​ገኝ ዘንድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ፥ ሰላ​ምን እንደ ወንዝ፥ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ክብር እን​ደ​ሚ​ጐ​ርፍ ፈሳሽ እመ​ል​ስ​ላ​ታ​ለሁ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ላይ እያ​ስ​ቀ​መጡ ያቀ​ማ​ጥ​ሏ​ቸ​ዋል።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።


ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች