የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻቸው መጥተው እንዲያግዟቸውም በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስመጥ ጀመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው ጠቀሱ፤ መጥተውም ሁለቱ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 5:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጠ​ላ​ት​ህን አህያ ከጭ​ነቱ በታች ወድቆ ብታ​ገ​ኘው አት​ለ​ፈው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ጋር ለማ​ን​ሣት ርዳው።


ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ።


እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸ​ውም ባደ​ረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስ​ኪ​ቀ​ደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ በር​ና​ባስ ሳው​ልን ሊፈ​ልግ ወደ ጠር​ሴስ ሄደ፤ በአ​ገ​ኘ​ውም ጊዜ ወደ አን​ጾ​ኪያ ወሰ​ደው።


ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ።


ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።