Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻቸው መጥተው እንዲያግዟቸውም በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስመጥ ጀመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው ጠቀሱ፤ መጥተውም ሁለቱ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚጠላህ ሰው አህያ ከጭነቱ ክብደት የተነሣ ወድቆ ብታገኝ፥ አህያውን ከወደቀበት ለማንሣት እንዲችል እርዳው እንጂ አልፈኸው አትሂድ።


ወዳጆች ሳይሆኑ ወዳጆች መስለው የሚታዩ አሉ፤ እውነተኛ ወዳጅ ግን ከወንድም ይበልጣል።


ከሕዝቡም ተለይተው ተሳፍሮበት በነበረው ጀልባ ኢየሱስን ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎችም ጀልባዎች አብረው ነበሩ።


መረቡን በጣሉ ጊዜ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ።


ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ፥ “ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ ወደ እኔ አትቅረብ!” አለው።


ከዚህ በኋላ በርናባስ ሳውልን ለመፈለግ ወደ ጠርሴስ ሄደ።


ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህ ዐይነት የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች