Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ገላትያ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ወን​ድ​ምን ስለ ማጽ​ና​ናት

1 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።

2 ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ።

3 አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።

4 ለሌላ ያይ​ደለ ለራሱ መመ​ኪያ እን​ዲ​ሆ​ነው ሁሉም ሥራ​ዉን ይመ​ር​ምር።

5 ሁሉም ሸክ​ሙን ይሸ​ከ​ማ​ልና።

6 ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።

7 አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ብት አይ​ኑር፤ ሰውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ያጭ​ዳል።

8 በሥ​ጋው የሚ​ዘራ ሞትን ያጭ​ዳል፤ በመ​ን​ፈ​ሱም የሚ​ዘራ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያጭ​ዳል።

9 በጎ ሥራ መሥ​ራ​ትን ቸል አን​በል፥ በጊ​ዜው እና​ገ​ኘ​ዋ​ለ​ንና።

10 እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


ምክ​ርና ቡራኬ

11 በእጄ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ እዩ።

12 ለሰው ፊት ሊያ​ደሉ የሚ​ወዱ እነ​ዚያ እን​ድ​ት​ገ​ዘሩ ያስ​ገ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀል እን​ዳ​ት​ከ​ተሉ ነው።

13 የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም።

14 እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።

15 በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።

16 ይህን ሕግ ለሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች ሰላ​ምና ይቅ​ርታ ይሁን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች በሆኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ይሁን።

17 እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።

18 ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላ​ትያ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች