የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚህ ሁሉ ከተ​ረ​ፋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አግ​ብ​ተ​ዋ​ልና፤ ይህቺ ግን ከድ​ህ​ነቷ ያላ​ትን ጥሪ​ቷን ሁሉ አገ​ባች።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ሰዎች የሰጡት ከትርፋቸው ላይ ሲሆን፣ እርሷ ግን የሰጠችው ከጕድለቷ ያላትን መተዳደሪያዋን በሙሉ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ መዝገቡ አስቀምጠዋልና፤ እርሷ ግን እየጐደላት የነበራትን ንብረት ሁሉ ሰጠች፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱ የሰጡት ከሀብታቸው የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 21:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው።


ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህቺ ድሃ መበ​ለት ከሁሉ ይልቅ አብ​ዝታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አገ​ባች።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።