Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ ሊፈውሳትም የቻለ ማንም አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:43
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህቺ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይ​ጣን ከአ​ሰ​ራት ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነው፤ እር​ስ​ዋስ በሰ​ን​በት ቀን ከእ​ስ​ራቷ ልት​ፈታ አይ​ገ​ባ​ምን?”


ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ።


ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐ​በ​ጣት አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ ጐባ​ጣም ነበ​ረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አት​ች​ልም ነበር።


ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ጋኔን ያደ​ረ​በት ሰው ከከ​ተማ ወጥቶ ተገ​ና​ኘው፤ ልብ​ሱ​ንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመ​ቃ​ብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይ​ገ​ባም ነበር፤


እስ​ት​ን​ፋሱ በአ​ፍ​ን​ጫው ያለ​በ​ትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈ​ጠ​ራል?


አሳም በነ​ገሠ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት እግ​ሩን ታመመ፤ ደዌ​ውም ጸና​በት፤ ነገር ግን በሕ​ማሙ ጊዜ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ገም።


ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።


ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር።


አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።”


በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።


የሚ​ረ​ዳ​ው​ንም አያ​ግኝ፤ ለድሃ አደግ ልጆ​ቹም የሚ​ራራ አይ​ኑር።


እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።


ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው።


ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።


ቀር​ባም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆመ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ ዳሰ​ሰች፤ ያን​ጊ​ዜም የደ​ምዋ መፍ​ሰስ ቆመ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች