የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘን​ድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያች መን​ገድ ያልፍ ዘንድ አለ​ውና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 19:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ብሩ​ንና ወር​ቁን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ እን​ዲ​በዛ አደ​ረ​ገው፤ የዝ​ግ​ባም እን​ጨት ብዛት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ሆነ።


በቈ​ላ​ውም ውስጥ ባሉት በወ​ይ​ራ​ውና በሾ​ላው ዛፎች ላይ ጌድ​ራ​ዊው በአ​ል​ሐ​ናን ሹም ነበረ፤ በዘ​ይ​ቱም ቤቶች ላይ ኢዮ​አስ ሹም ነበረ፤


ንጉ​ሡም ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ንም እን​ጨት በብ​ዛት በቆላ እን​ደ​ሚ​ገኝ ሾላ በይ​ሁዳ አኖረ።


ንጉ​ሡም ወር​ቁ​ንና ብሩን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ው​ንም እን​ጨት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ብዛት አደ​ረ​ገው።


“ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።”


አሞ​ጽም መልሶ አሜ​ስ​ያ​ስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባ​ቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነ​ቢይ ልጅ አይ​ደ​ለ​ሁም፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣት ታህል እም​ነት ብት​ኖ​ራ​ችሁ ይህ​ችን ሾላ ከሥ​ርሽ ተነ​ቅ​ለሽ በባ​ሕር ውስጥ ተተ​ከዪ ብት​ሉ​አት ትታ​ዘ​ዝ​ላ​ች​ኋ​ለች።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ያየው ዘንድ፥ ማን እንደ ሆነም ያውቅ ዘንድ ይሻ ነበር፤ የሰው ብዛ​ትም ይከ​ለ​ክ​ለው ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበ​ርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ​ዚያ በደ​ረሰ ጊዜ አሻ​ቅቦ አየ​ውና፥ “ዘኬ​ዎስ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤ​ትህ እውል ዘንድ አለ​ኝና” አለው።


ሰውም ተጨ​ና​ንቆ ነበ​ርና የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​በት አጡ፤ ወደ ሰገ​ነ​ትም ወጡ፤ ጣራ​ው​ንም አፍ​ር​ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ፊት ከነ​አ​ል​ጋው አወ​ረ​ዱት።