Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሰውም ተጨ​ና​ንቆ ነበ​ርና የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​በት አጡ፤ ወደ ሰገ​ነ​ትም ወጡ፤ ጣራ​ው​ንም አፍ​ር​ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ፊት ከነ​አ​ል​ጋው አወ​ረ​ዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ቤቱ ውስጥ ማስገባት ስላቃታቸው፣ ጣራው ላይ ወጥተው የቤቱን ክዳን በመንደል በሽተኛውን ከነዐልጋው በሕዝቡ መካከል ቀጥታ ኢየሱስ ፊት አወረዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ እርሱን ለማስገባት ምንም ዓይነት መንገድ ባለማግኘታቸው ወደ ሰገነቱ ወጡ፤ የጣራውንም ጡብ አሳልፈው በመካከላቸው ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አወረዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ቤት ማግባት አቃታቸው፤ ስለዚህ ወደ ጣራ ላይ ይዘውት ወጡ፤ ጣራውንም ከፍተው በመካከሉ አውርደው ሽባውን ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አኖሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ስለ ሕዝቡም ብዛት እንዴት አድርገው እንዲያገቡት ሲያቅታቸው፥ ወደ ሰገነቱ ወጡ የጣራውንም ጡብ አሳልፈው በመካከል በኢየሱስ ፊት ከነአልጋው አወረዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:19
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤቶ​ችና የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረ​ከሱ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ያም በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ ያጠ​ኑ​ባ​ቸው፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸው ቤቶች ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።”


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤


ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ።


“አዲስ ቤት በሠ​ራህ ጊዜ ማንም ከእ​ርሱ ወድቆ በቤ​ትህ ግድያ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ለሰ​ገ​ነ​ትህ መከታ አድ​ር​ግ​ለት።


ከባማ ኮረ​ብ​ታም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወረዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል በሰ​ገ​ነቱ ላይ መኝታ አዘ​ጋ​ጀ​ለት፤ እር​ሱም ተኛ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች