ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
ኢያሱ 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከተማዪቱም ሰዎች ወጡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ተቀበሉአቸው፤ እርሱ ግን ከከተማዪቱ በስተኋላ እንደ ተደበቁ አያውቅም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋይ ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማዪቱ ወንዶች ሁሉ ማልደው በመገሥገሥ፣ እስራኤልን ለመውጋት ከዓረባ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ስፍራ መጡ፤ ንጉሡ ግን ከከተማዪቱ በስተጀርባ ያደፈጠ ኀይል የሚጠባበቀው መሆኑን አያውቅም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋይም ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ቸኩለው በማለዳ ተነሡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወጡ፤ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ቸኩለው በማለዳ ተነሡ፥ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ወዳለው ወደ አንድ ስፍራ እስራኤልን በሰልፍ ለመገናኘት ወጡ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር። |
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?”
በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በምዕራብ በኩል በኤርትራ ባሕር አጠገብ በፋራንና በጦፌል፥ በላባንና በአውሎን፥ በካታኪሪሲያም መካከል፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ፥ የነገራቸው ቃላት እኒህ ናቸው።
ሕዝቡም ሁሉ ሠራዊቶቻቸውን በከተማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳርቻውም እስከ ከተማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።
የሀገሪቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእስራኤልንም ልጆች ተከትለው አሳደዱአቸው፤ ከከተማዪቱም እንዲርቁ አደረጓቸው።
እኔ፥ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማዪቱ እንቀርባለን፤ የጋይም ሰዎች እኛን ሊገናኙ እንደ ፊተኛው በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤