ኢያሱ 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የጋይም ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ቸኩለው በማለዳ ተነሡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወጡ፤ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የጋይ ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማዪቱ ወንዶች ሁሉ ማልደው በመገሥገሥ፣ እስራኤልን ለመውጋት ከዓረባ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ስፍራ መጡ፤ ንጉሡ ግን ከከተማዪቱ በስተጀርባ ያደፈጠ ኀይል የሚጠባበቀው መሆኑን አያውቅም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የጋይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከተማዪቱም ሰዎች ወጡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ተቀበሉአቸው፤ እርሱ ግን ከከተማዪቱ በስተኋላ እንደ ተደበቁ አያውቅም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ቸኩለው በማለዳ ተነሡ፥ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ወዳለው ወደ አንድ ስፍራ እስራኤልን በሰልፍ ለመገናኘት ወጡ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |