Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 24:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እስከዚያ ጊዜ ድረስም ምን እንደሚመጣ ሳያውቁ ድንገት የጥፋት ውሃ እንዳጥለቀለቃቸው፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንደዚሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉን እስኪወስድ ድረስ እንዳላወቁት፥ የሰው ልጅ መምጣትም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከ ወሰዳቸው ድረስ አላወቁም ነበር፤ የሰው ልጅ አመጣጥም ልክ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 24:39
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም።


የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።


‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”


ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውሃ ተጋጥማ በውሃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤


እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


አን​ቺን ይጥ​ሉ​ሻል፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ጋር ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ድን​ጋ​ይ​ንም በደ​ን​ጋይ ላይ አይ​ተ​ዉ​ል​ሽም፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ሽን ዘመን አላ​ወ​ቅ​ሽ​ምና።”


ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


“መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ዘበቱብኝ፥ እኔም አላወቅሁም። ከእኔ ጋር የሚሄዱትን መጥቼ እፈልግ ዘንድ መቼ ጧት ይሆናል?” ትላለህ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የተ​መ​ረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባ​ዖን አን​ጻር መጡ፤ ውጊ​ያ​ውም በር​ትቶ ነበር፤ መከ​ራም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አላ​ወ​ቁም ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


በም​ድር ላይ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ፥ እስ​ከ​ሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰ​ውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደ​መ​ሰሰ፤ ከም​ድ​ርም ተደ​መ​ሰሱ። ኖኅም አብ​ረ​ውት በመ​ር​ከብ ከነ​በ​ሩት ጋር ብቻ​ውን ቀረ።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።


የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤


በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች