የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን እርም በሆ​ነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እር​ሱም የከ​ርሚ ልጅ፥ የዘ​ን​በሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆ​ነው ነገር ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን ግን ዕርም የሆነውን ነገር ለራሳቸው በመውሰድ በደሉ፤ ይህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው አካን የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ ዕርም ከሆነው ነገር ስለ ወሰደ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ የጌታም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ግን የተከለከሉ ነገሮችን በተመለከተ ታማኞች ሆነው አልተገኙም፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ዓካን፥ የከርሚ ልጅ፥ የዘብዲ የልጅ ልጅ፥ የዛራ ልጅ ከተከለከሉት ነገሮች በመውሰድ በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ቊጣ አስነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 7:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የያ​ዕ​ቆብ ልጆ​ችም ወደ ሞቱት ገብ​ተው እኅ​ታ​ቸው ዲናን ያስ​ነ​ወ​ሩ​ባ​ትን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ዘረፉ፤


ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንና ይሁ​ዳን ቍጠር” ብሎ በላ​ያ​ቸው አስ​ነ​ሣው።


ወደ ስውር ቦታም በደ​ረሱ ጊዜ ከእ​ጃ​ቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በተ።


ይህም ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመጣ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ትተው ባዕድ አም​ላ​ክ​ንና ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለኩ፤ በዚ​ያም ወራት በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ቍጣ ወረደ።


እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ኀጢ​አ​ታ​ችን በራ​ሳ​ችን ላይ በዝ​ቶ​አ​ልና፥ በደ​ላ​ች​ንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ​አ​ልና አም​ላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ራ​ማ​ለሁ።


እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ክፋ​ትህ ይጎ​ዳ​ዋል፤ ለሰ​ውም ልጅ ጽድ​ቅህ ይጠ​ቅ​መ​ዋል።


ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።


ሙሴም አሮ​ንን፥ ልጆ​ቹ​ንም አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን፥ “እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ራሳ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አት​ቅ​ደዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ቃ​ጠ​ላ​ቸው ማቃ​ጠል ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ያል​ቅሱ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ሁሉ የሚ​ለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠ​ዊ​ያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ ትክ​ዱት ዘንድ ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀጢ​አት ምን​ድን ነው?


እና​ንተ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትታ​ች​ኋል፤ ዛሬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ብታ​ምፁ ነገ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ናል።


የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመ​ው​ሰድ ኀጢ​አ​ትን ስለ ሠራ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ ቍጣ አል​ወ​ረ​ደ​ምን? እር​ሱም ብቻ​ውን ቢበ​ድል በኀ​ጢ​አቱ ብቻ​ውን ሞተን?”