ኢያሱ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባት ካህናት፣ ሰባት ቀንደ መለከት ተሸክመው በታቦቱ ፊት ይውጡ፤ በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ መለከት እየነፉ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዳቸው እምቢልታ የያዙ ሰባት ካህናት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ በሰባተኛው ቀን ካህናቱ እምቢልታ እየነፉ አንተና ወታደሮችህ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ትዞሩአታላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፥ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። |
ብላቴናውንም፥ “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። ብላቴናውም ተመልክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤልያስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመላለስ” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።
ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ተጠመቅ፤ ሰውነትህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።
ንዕማንም ወረደ፤ የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ተጠመቀ፤ ሰውነቱም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሰውነት ሆኖ ተመለሰ፤ ንጹሕም ሆነ።
እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ሌዋውያንም፥ ከቀዓት ልጆችና ከቆሬ ልጆች የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ።
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ እርሱም የሚቃጠልን መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ ያሳርግላችሁ። ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልይ፥ እኔም ፊቱን እቀበላለሁ። ስለ እርሱ ባይሆን ባጠፋኋችሁ ነበር። በባሪያዬ በኢዮብ ላይ ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና።”
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦርም የጠፉ፥ በግብፅ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሰባቱም ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፤ ተዋጊዎችም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀሩትም ሕዝብ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።
አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።
ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማዪቱም ቅጥር ይወድቃል፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ፊት ለፊት እየሮጠ ይገባባታል።”
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር፥ ከሙታንም በኵር፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።
ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።
በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።