የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት የጀመሩትም በዚያን ቀን ማግስት ነበር፤ የተመገቡትም የተጠበሰ እሸትና ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 5:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ጀ​ራ​ው​ንም፥ የተ​ጠ​በ​ሰ​ው​ንም እሸት፥ ለም​ለ​ሙ​ንም እሸት የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቍር​ባን እስ​ከ​ም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ አት​ብሉ። ይህ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።


በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።


ወደ​ማ​መ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ንተ የም​ድ​ሪ​ቱን እን​ጀራ በበ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።


በነ​ጋ​ውም ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዳግ​መኛ መና አላ​ገ​ኙም፤ በዚ​ያው ዓመት የፊ​ኒ​ቆ​ንን ምድር ፍሬ ሰበ​ሰቡ።