Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት የጀመሩትም በዚያን ቀን ማግስት ነበር፤ የተመገቡትም የተጠበሰ እሸትና ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 5:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህንንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ከማቅረባችሁ በፊት ከአዲሱ እህል ጥሬውን ወይም የተቈላውን ወይም እንጀራ ጋግራችሁ አትብሉ። ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኑር።


በዐሥራ አምስተኛው ቀን የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ከዚያን በኋላ እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትመገባላችሁ።


ከምድሪቱ የሚመረተውን ነገር ሁሉ በምትመገቡበት ወቅት ከእርሱ ላይ ጥቂት በማንሣት ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ አቅርቡ፤


እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ ባለው ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፥ ከወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ፤


ከምድሪቱ የሚገኘውን ምግብ መብላት ከጀመሩበት ቀን አንሥቶ መና መዝነቡን አቋረጠ፤ እስራኤላውያንም ከዚያን በኋላ ያን መና ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያን ጊዜ አንሥቶ በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት ጀመሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች