የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን እስካሁን እንዳደረጋችሁት ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አጥብቃችሁ ያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት ግን ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ተጠጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይልቅስ እስከ አሁን እንዳደረጋችሁት ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሁኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተጠጉ እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 23:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዛ​ቱን ጠበቀ።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል፤ በስ​ሙም ማል።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ፤ እር​ሱ​ንም ፍሩ፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቁ፤ ቃሉ​ንም ስሙ፥ እር​ሱ​ንም ተማ​ጠ​ኑት።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


እና​ንተ ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሁላ​ችሁ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አል​ሰ​ማ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​አ​ጠ​ፋ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተም እን​ዲሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።


ብቻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ታደ​ርጉ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትወ​ድዱ ዘንድ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ችሁ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።”


በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤


እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ላ​ቆ​ች​ንና ኀይ​ለ​ኞ​ችን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የተ​ቋ​ቋ​ማ​ችሁ በፊ​ታ​ችሁ ማንም የለም።