የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከፊ​ታ​ችሁ እስ​ኪ​ደ​መ​ሰሱ ድረስ ያጠ​ፋ​ላ​ች​ኋል፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም እነ​ር​ሱ​ንና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ የዱር አራ​ዊ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ ያስወግዳቸዋል፤ ከፊታችሁም ያሉበትን ስፍራ ያስለቅቃቸዋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁም ተስፋ መሠረት ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ አምላካቸሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ገፍቶ ያስወጣቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል፤ ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እነርሱን ነቃቅሎ ያጠፋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁም ተስፋ መሠረት ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላካቸሁም እግዚአብሔር እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 23:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በመ​ን​ገድ ይጠ​ብ​ቅህ ዘንድ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ል​ህም ስፍራ ያገ​ባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መል​አ​ኬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ።


መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል።


በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው።


እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም።