የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ሰዎቹን ጣራ ላይ አውጥታ በረበረበችው የተልባ እግር ውስጥ ደብቃቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፤ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታ በዚያ በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፥ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 2:6
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ሴቲ​ቱም ዳውጃ ወስዳ በጕ​ድ​ጓዱ አፍ ላይ ዘረ​ጋ​ች​በት፤ የተ​ፈ​ተገ እህ​ልም በላዩ አሰ​ጣ​ች​በት፤ ያወ​ቃ​ቸ​ውም የለም።


ኤል​ዛ​ቤል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ፥ መቶ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ወስጄ፥ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እን​ጀ​ራና ውኃ የመ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውን፥ ይህን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አል​ሰ​ማ​ህ​ምን?


ኤል​ዛ​ቤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ አብ​ድዩ መቶ​ውን ነቢ​ያት ወስዶ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እን​ጀ​ራና ውኃ ይመ​ግ​ባ​ቸው ነበር።


የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት ኢዮ​ሳ​ቡ​ሄም የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል ሰርቃ ወሰ​ደ​ችው፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱ​ንም ወደ እል​ፍኝ ወሰ​ደች፤ ከጎ​ቶ​ል​ያም ሸሸ​ገ​ችው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​ት​ምም።


ሴቲ​ቱም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ መል​ካ​ምም እን​ደ​ሆነ በአዩ ጊዜ ሦስት ወር ሸሸ​ጉት።


ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።


በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤


“አዲስ ቤት በሠ​ራህ ጊዜ ማንም ከእ​ርሱ ወድቆ በቤ​ትህ ግድያ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ለሰ​ገ​ነ​ትህ መከታ አድ​ር​ግ​ለት።


እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።


ሙሴ በተ​ወ​ለደ ጊዜ በእ​ም​ነት ሦስት ወር በአ​ባቱ ቤት ሸሸ​ጉት፤ ሕፃኑ መል​ካም እንደ ሆነ አይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ የን​ጉ​ሥ​ንም ትእ​ዛዝ አል​ፈ​ሩም።


እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?


በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው።


ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።


እነ​ዚ​ህም ሳይ​ተኙ ሴቲቱ ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰገ​ነቱ ወጣች።


ኢያ​ሪ​ኮን ሊሰ​ልሉ ኢያሱ የላ​ካ​ቸ​ው​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊ​ቱን ረዓ​ብን፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤተ ሰብ፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ ኢያሱ አዳ​ና​ቸው፤ እር​ስ​ዋም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጣ​ለች።