Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኢያ​ሪ​ኮን ሊሰ​ልሉ ኢያሱ የላ​ካ​ቸ​ው​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊ​ቱን ረዓ​ብን፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤተ ሰብ፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ ኢያሱ አዳ​ና​ቸው፤ እር​ስ​ዋም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጣ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢያሪኮን እንዲሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን ሰዎች ስለ ደበቀች፣ ጋለሞታዪቱን ረዓብን፣ ቤተ ሰቧንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ አዳናቸው፤ እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤላውያን መካከል ትኖራለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢያሪኮንም ሊሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች አመንዝራይቱን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው፤ እርሷም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ነገር ግን ጋለሞታይቱ ረዓብ ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ የላካቸውን ሁለቱን ሰላዮች ደብቃ ከሞት ስላዳነች እርሱ እርስዋን፥ ቤተ ዘመዶችዋንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ከሞት አተረፈ፤ የእርስዋም ዘሮች እስከ አሁን ድረስ በእስራኤል ምድር ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውንም መልክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው፥ እርስዋም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 6:25
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዘማ ረአ​ብም በእ​ም​ነት ከከ​ሓ​ዲ​ዎች ጋር አል​ጠ​ፋ​ችም፤ ጕበ​ኞ​ችን በሰ​ላም ተቀ​ብላ ሰው​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ችና።


እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?


ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤


እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ።


ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤


እነሆ፥ እኛ ወደ ሀገሩ በገ​ባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወ​ረ​ድ​ሽ​በት መስ​ኮት በኩል እሰ​ሪው፤ አባ​ት​ሽ​ንም፥ እና​ት​ሽ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ሽ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ሽ​ንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብ​ስቢ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች