ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል።
ኢያሱ 19:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ይዞራል፤ ከዚያም ወደ ያቃና ይወጣል፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፤ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፥ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ። |
ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል።
ድንበራቸውም ወደ ታቦርና ወደ ሰሌም፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቤተሳሚስ ይደርሳል፤ የድንበራቸው መውጫም ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸውም።
ድንበራቸውም ከመሐላም፥ ከሞላም፥ ከቤሴሜይን፥ ከአርሜ፥ ከናቦቅና፥ ከኢያፍታሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ።