Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የተ​መ​ሸ​ጉ​ትም የሲ​ዶና ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማ​ታ​ዳ​ቄት፥ ቄሬት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እንዲሁም የተመሸጉት ከተሞች ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ራቃት፥ የገሊላ ባሕር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፥ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:35
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥


በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


አራ​ዲ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ር​ዮ​ንን፥ አማ​ቲ​ንን ወለደ። ከዚ​ህም በኋላ የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ነገድ ተበ​ተኑ።


ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ ታንኳይቱንም አስጠጉ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ቤት​ሀ​ራም፥ ቤት​ን​ምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ቅሬታ ነበረ። ድን​በ​ሩም ዮር​ዳ​ኖ​ስና በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የኬ​ኔ​ሬት ባሕር ወዲ​ያ​ኛው ዳርቻ ነበረ።


ከተ​ራ​ራው እስከ ተራ​ራው ድረስ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ እስከ ኤማ​ትም ይደ​ር​ሳል፤ የዳ​ር​ቻ​ውም መውጫ በሰ​ረ​ደክ ይሆ​ናል፤


ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።


ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል።


አር​ሜት፥ አራ​ሂን፥ አሦር፥


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች