Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፥ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:34
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ንፍታሌም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በጌታ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነው፤ በእግዚአብሔር በረከትም ተሞልቶአል፤ ግዛቱም እስከ ባሕሩና ወደ ደቡብ የተዘረጋ ነው።”


ከሣሪድም ባሻገር በምሥራቅ በኩል ወደ ኪስሎት ታቦር አልፎ እስከ ዳብራትና እስከ ያፊዓ ይደርሳል፤


ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤


ድንበሩም ከሔሌፍ በመነሣት በአዳሚኔቄብና በያሚኒያ በኩል መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ እስከ ላቁም ድረስ እስከ ዳዕናኒም ወርካ ይዘልቃል።


እንዲሁም የተመሸጉት ከተሞች ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ራቃት፥ የገሊላ ባሕር፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች