Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፥ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:34
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በሞገስ ጠግቧል፥ የጌታንም በረከት ተሞልቶአል፥ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።”


ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፤ ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፤


ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤት-ሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መጨረሻ ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ በጸዕነኒም ካለው ከባሉጥ ዛፍ፥ ከአዳሚ-ኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መጨረሻውም በዮርዳኖስ ነበረ።


የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች