ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት።
ኢያሱ 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፤ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምንጭም ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸው ድንበር ከራፋይም ሸለቆ በስተሰሜን ባለው በሄኖም ሸለቆ ትይዩ ቍልቍል ወደ ኰረብታው ግርጌ ይወርዳል፤ ከዚያም ከኢያቡሳውያን ከተማ በደቡብ በኩል ባለው ተረተር አድርጎ ወደ ሄኖም ሸለቆ በመውረድ እስከ ዓይንሮጌል ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ወገን በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ድንበሩ የሔኖም ልጅ ሸለቆ ትይዩ ወደ ሆነው ተራራ ግርጌ ይወርዳል፤ እርሱም ከራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ከዚያም ወደ ሔኖም ሸለቆ ይወርድና በኢያቡሳውያን ተረተር ጐን አድርጎ ወደ ኤንሮጌል ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፥ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ። |
ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት።
አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን፥ ጠቦቶችንም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም አገልጋዮች፥ የይሁዳንም ኀያላን ሁሉ ጠራ።
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለምስሉ ሠዋ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
እንዲህም ትላቸዋለህ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ማድጋ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀበሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።
ስለዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ይሁዳን ወደ ኀጢአት እንዲያገቡት፥ ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን መሠዊያዎች ለበዓል ሠሩ።”
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሴዎናውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።
ሰውዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፤ ተነሥቶም ሄደ፤ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፤ ዕቅብቱም ከእርሱ ጋር ነበረች።