ኢያሱ 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴም ልጆች ድንበር በሐነት ልጆች ፊት ያለው ዴላናታ ነው። በኢያሚንና በኢያሲብ ድንበር በተፍቶት ምንጭ ላይ ያልፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴም ግዛት ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ነበረ፤ ድንበሩም በቀኝ በኩል ወደ ዓይንታጱዋ ሰዎች አለፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናሴ የርስት ይዞታ ከአሴር ተነሥቶ በሴኬም በስተ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሚክመታት ይደርስ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በማለፍ የዔንታፑዓሕን ሕዝብ ይጨምራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴም ድንበር ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ነበረ፥ ድንበሩም በቀኝ በኩል ወደ ዓይንታጱዋ ሰዎች አለፈ። |
እርሱም፥ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። ወደ ኬብሮንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬምም መጣ።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ደግሞም ጋዜርንና መሰማሪያዋን፤
የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ተቀብለዋልና፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና።
በንፍታሌም ባለው በተራራማው ሀገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው ሀገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው ሀገር ኬብሮን የምትባለውን የአርቦቅን ከተማ ለዩ።
ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፥ አለቆቻቸውንም፥ ጸሓፊዎቻቸውንም፥ ፈራጆቻቸውንም ጠራቸው። በእግዚአብሔርም ፊት አቆማቸው።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አፅም ያዕቆብ በሰቂማ ከሚኖሩ ከአሞራውያን በመቶ በጎች በገዛው ለዮሴፍ ድርሻ አድርጎ በሰጠው እርሻ በአንዱ ክፍል በሰቂማ ቀበሩት።
የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፤ ለእነርሱም፥ ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦