Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 17:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የም​ናሴ ሴቶች ልጆች በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ የገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች ሆኖ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የምናሴ ነገድ ሴት ልጆች ከወንዶቹ ጋራ ርስት ተካፍለዋልና። የገለዓድ ምድር ግን ለቀሩት የምናሴ ዘሮች ተሰጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ስለወረሱ፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ስለሆነ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሴቶች ዘሮቹ እንደ ወንዶች ዘሮቹ የርስት ድርሻ ስለ ተቀበሉ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ዘሮች ተሰጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ተቀብለዋልና፥ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 17:6
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከን​ፍ​ታ​ሌም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለም​ናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


ሙሴም ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት ሰጣ​ቸው፤


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥


በባ​ሳ​ንም ያሉት የዐግ መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች፥ አስ​ጣ​ሮ​ትና ኤድ​ራ​ይን ነበረ። እነ​ዚ​ህም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች ሆኑ፤ ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች እኩ​ሌ​ታም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤


የም​ና​ሴም ልጆች ድን​በር በሐ​ነት ልጆች ፊት ያለው ዴላ​ናታ ነው። በኢ​ያ​ሚ​ንና በኢ​ያ​ሲብ ድን​በር በተ​ፍ​ቶት ምንጭ ላይ ያል​ፋል።


ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሙሴ በባ​ሳን ውስጥ ርስት ሰጥ​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ ለቀ​ረው ለእ​ኩ​ሌ​ታው ግን ኢያሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ሰጣ​ቸው። ኢያ​ሱም ወደ ቤታ​ቸው በአ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ ብሎ መረ​ቃ​ቸው፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች