Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ያወ​ጡ​ትን የዮ​ሴ​ፍን አፅም ያዕ​ቆብ በሰ​ቂማ ከሚ​ኖሩ ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን በመቶ በጎች በገ​ዛው ለዮ​ሴፍ ድርሻ አድ​ርጎ በሰ​ጠው እርሻ በአ​ንዱ ክፍል በሰ​ቂማ ቀበ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እስራኤላውያን ከግብጽ ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም፣ ያዕቆብ ከሰኬም አባት ከኤሞር በመቶ ሰቅል ብር በገዛው በሴኬም ምድር ተቀበረ፤ ይህችም የዮሴፍ ዘሮች ርስት ሆነች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ ብር በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በግ በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት፥ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:32
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ አጥ​ን​ቴን ከዚህ አን​ሥ​ታ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማ​ላ​ቸው።


ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።


ሙሴም የዮ​ሴ​ፍን ዐጽም ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጐ​ብ​ኘ​ትን በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ ዐጽ​ሜን ውሰዱ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።


ወደ ሴኬ​ምም አፍ​ል​ሰው አብ​ር​ሃም ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በገ​ን​ዘቡ በገ​ዛው መቃ​ብር ቀበ​ሩ​ዋ​ቸው።


ዮሴ​ፍም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ፥ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ መው​ጣት በእ​ም​ነት ዐሰበ፤ ዐጽ​ሙ​ንም ትተው እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘዘ።


ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ።


እኔም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን እጅ በሰ​ይ​ፌና በቀ​ስቴ የወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ምርኮ ለአ​ንተ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ የተ​ሻ​ለ​ውን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች