ወዲያ ወዲህም እስኪመላለስ ድረስ ሰማዩ በደመናና በነፋስ ጨለመ፤ ትልቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክዓብም በሰረገላ ተቀምጦ እያለቀሰ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ።
ኢያሱ 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ተራራማው የኤፍሬም ሀገር አይበቃንም፤ በሸለቆው ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤትሳንና በመንደሮችዋ፥ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የተመረጡ ፈረሶችና ሰይፍ አሏቸው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍም ዘሮች፣ “ኰረብታማው አገር አይበቃንም፤ ደግሞም በሜዳው ላይ ያሉት በቤትሳንና በሰፈሮቿ፣ እንዲሁም በኢይዝራኤል ሸለቆ የሚኖሩት ከነዓናውያን ሁሉ የብረት ሠረገሎች አሏቸው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉት፦ “ተራራማው አገር አይበቃንም፤ በሸለቆውም ውስጥ የሚኖሩት፥ በቤትሳና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ የሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰረገሎች አላቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ኮረብታማይቱ አገር ለእኛ በቂ አይደለችም፤ ከዚህም ሁሉ ጋር በኢይዝራኤል ሸለቆ በቤትሻንና በዙሪያዋ ባሉት ታናናሽ ከተሞችና በሜዳማው አገር የሚኖሩ ከነዓናውያን ብዙ የብረት ሠረገሎች አሉአቸው” ሲሉ መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍም ልጆች፦ ተራራማው አገር አይበቃንም፥ በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤትሳና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰረገሎች አላቸው አሉት። |
ወዲያ ወዲህም እስኪመላለስ ድረስ ሰማዩ በደመናና በነፋስ ጨለመ፤ ትልቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክዓብም በሰረገላ ተቀምጦ እያለቀሰ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ።
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት፤ እየጠበቃቸውም ተቀመጠ። ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ነበሩ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥተውም ሰማርያን ከበቧት፥ ወጓትም።
የሶርያም ንጉሥ አገልጋዮች እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብንዋጋቸው ድል እናደርጋቸው ነበር።
ከቤትሳን ጀምሮ እስከ አቤልምሖላና እስከ ዮቅምዓም ማዶ ድረስ በታዕናክና በመጊዶ በጸርታንም አጠገብ በኢይዝራኤል በታች ባለው በቤትሳን ሁሉ የአሒሉድ ልጅ በዓና ነበረ፤
የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆናልና ማንም፦ ይህች ኤልዛቤል ናት ይል ዘንድ አይችልም ብሎ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው” አለ።
ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ መጌዶና መንደሮችዋ፥ የመፌታ ሦስተኛ እጅና መንደሮችዋ ለምናሴ ነበሩ።
ኢያሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ተራራማው የኤፍሬም ሀገርም ከጠበባችሁ ወደ ዱር ወጥታችሁ መንጥራችሁ አቅኑአት” አላቸው።
ነገር ግን ተራራማው ሀገር ለእናንተ ይሆናል፤ ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩታላችሁ፤ ለእናንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የተመረጡ ፈረሶችና የብረት ሰረገሎች ቢሆኑላቸው፥ የበረቱ ቢሆኑም እናንተ እስክታጠፉአቸው ድረስ ትበረቱባቸዋላችሁ” አላቸው።
እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም።
ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝቡን ሁሉ ከአሕዛብ አሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።