Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ነገር ግን ተራ​ራ​ማው ሀገር ለእ​ና​ንተ ይሆ​ናል፤ ዱር እንኳ ቢሆ​ንም ትመ​ነ​ጥ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ና​ን​ተም ይሆ​ናል፤ ለከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ቢሆ​ኑ​ላ​ቸው፥ የበ​ረቱ ቢሆ​ኑም እና​ንተ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ ትበ​ረ​ቱ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ነገር ግን ደን የለበሰው ኰረብታማው አገር የእናንተ ነው፤ ሄዳችሁ መንጥሩት፣ ዳር ድንበሩ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ከነዓናውያን የብረት ሠረገላ ቢኖራቸውና ብርቱዎች ቢሆኑም እንኳ ከዚያ ታስወጧቸዋላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢኖሩአቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ ኮረብታማው አገር የእናንተ ይሆናል፤ ጫካም ቢሆን መንጥራችሁ ዳር እስከ ዳር የራሳችሁ ርስት አድርጉት፤ ስለ ከነዓናውያን ጉዳይ የሆነ እንደሆን ምንም የብረት ሠረገሎች ቢኖራቸውና ምንም ብርቱዎች ቢሆኑ ነቃቅላችሁ ልታባርሩአቸው ትችላላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፥ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢሆኑላቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 17:18
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ቀስ​ቶ​ቻ​ቸው በኀ​ይል ተቀ​ጠ​ቀጡ፤ የእ​ጆ​ቻ​ቸው ክንድ ሥርም በያ​ዕ​ቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚ​ያም በአ​ባ​ትህ አም​ላክ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን አጸ​ናው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ወደ በረሓ ወጡ፤ በኤ​ፍ​ሬ​ምም በረሓ ተዋ​ጓ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀን​ዶቹ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ናቸው፤ በእ​ነ​ርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ ይወ​ጋል፤ የኤ​ፍ​ሬም እልፍ አእ​ላ​ፋት፥ የም​ና​ሴም አእ​ላ​ፋት እነ​ርሱ ናቸው።


አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው።


ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።


ኢያ​ሱም ለዮ​ሴፍ ልጆች፥ “እና​ንተ ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ጽኑ ኀይ​ልም ከአ​ላ​ችሁ አንድ ዕጣ ብቻ አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች