Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲሁም በይሳኮርና በአሴር ውስጥ ቤትሳን፣ ይብለዓም፣ የዶር ሕዝብ፣ ዓይንዶር፣ ታዕናክና መጊዶ በዙሪያቸው ካሉ ሰፈሮቻቸው ጋራ የምናሴ ነበሩ፤ ሦስተኛውም ናፎት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በይሳኮርና በአሴር ግዛት ውስጥ ምናሴ ቤትሼንና መንደሮችዋ፥ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ የዶር ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ የዕንዶር ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ የታዕናክ ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ የመጊዶና ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ (በሦስተኛው ተራ ዶር የተባለው ናፋት ዶርም ይባላል)። እነዚህም ሁሉ የምናሴ ይዞታዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 17:11
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ና​ሴም ልጆች ዳርቻ ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ታዕ​ና​ክና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጊ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በላ​ድና መን​ደ​ሮ​ችዋ ነበሩ፤ በእ​ነ​ዚህ ያዕ​ቆብ የተ​ባለ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ የዮ​ሴፍ ልጆች ተቀ​መጡ።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።


ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።


ምና​ሴም የሰ​ቂ​ቶን ከተማ ቤት​ሶ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ኢቀ​ጸ​አ​ድ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዶ​ርን ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዮ​በ​ለ​ዓ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች፥ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የመ​ጊ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎች መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ይቀ​መጡ ዘንድ ጸኑ።


በፌ​ና​ድር ክፍል የም​ት​ሆን የኤ​ዶር ንጉሥ፥ በጋ​ልያ ክፍል የም​ት​ሆን የሐጌ ንጉሥ፥ የቲ​ርሣ ንጉሥ፥


ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤ በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር።


የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ስ​ታ​ሮት መቅ​ደስ ውስጥ አኖ​ሩት። ሬሳ​ው​ንም በቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉት።


ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ወደ እር​ስዋ ሄጄ እጠ​ይቅ ዘንድ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ ሴት ፈል​ጉ​ልኝ” አላ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ አን​ዲት ሴት በዓ​ይ​ን​ዶር አለች” አሉት።


በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥


በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።


ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።


ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዓኔ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ቤል​ዓ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ከቀ​ዓት ልጆች ወገን ለቀ​ሩት ሰጡ።


የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።


ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።


የአ​ዚፍ ንጉሥ፥ የቃ​ዴስ ንጉሥ፥


በደ​ቡብ በኩል ያለው ለኤ​ፍ​ሬም ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ያለ​ውም ለም​ናሴ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም ባሕር ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ወደ አሴር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ይሳ​ኮር ይደ​ር​ሳል።


እነ​ር​ሱም፥ “ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገር አይ​በ​ቃ​ንም፤ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ለሚ​ኖ​ሩት፥ በቤ​ት​ሳ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም ሸለቆ ለሚ​ኖ​ሩት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና ሰይፍ አሏ​ቸው” አሉት።


ዳዊ​ትም ሄደ፤ ሳአ​ል​ንም በጌ​ላ​ቡሄ በገ​ደ​ሉት ጊዜ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከሰ​ቀ​ሉ​አ​ቸው ስፍራ ከቤ​ት​ሳን አደ​ባ​ባይ ከሰ​ረ​ቁት ከኢ​ያ​ቤስ ገለ​ዓድ ሰዎች የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት ወሰደ።


ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች