የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
ኢያሱ 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ልጆችም የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ማጥፋት ተሳናቸው፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያች ሀገር ለመቀመጥ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የምናሴ ዘሮች እነዚህን ከተሞች መያዝ አልቻሉም፤ ከነዓናውያን የያዙትን ላለመልቀቅ ቍርጥ ሐሳብ አድርገው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴ ልጆች ግን የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ የምናሴ ልጆች ሕዝቡን አባረው እነዚያን ከተሞች ለመያዝ አልቻሉም፤ ስለዚህም ከነዓናውያን በዚያ መኖርን ቀጠሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴ ልጆች ግን የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ። |
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።