የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
ኢያሱ 15:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቃሮን ከመንደሮችዋና ከመሰማሪያዎችዋ ጋር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ከታናናሽ ከተሞችዋና መንደሮችዋ ጋር ዔቅሮን የምትባል ከተማ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፥ |
የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
የአዛጦን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤ የአስቀሎናም ሕዝብ ይጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፤ ከፍልስጥኤማውያን የቀሩትም ይጠፋሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤
ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ላኩአት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣች ጊዜ አስቀሎናውያን፥ “እኛንና ሕዝባችንን ልታስገድሉን የእስራኤልን አምላክ ታቦት ለምን አመጣችሁብን?” ብለው ጮኹ።
ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን።