ያዕቆብ ግን በሰፈሩ አደረ፤ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ማኅደር ብሎ ጠራው።
ኢያሱ 13:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸለቆው ውስጥ ደግሞ ቤትሀራምን፣ ቤትኒምራን፣ ሱኮትን፣ ዳፎንንና እስከ ኪኔሬት ባሕር ጫፍ የሚደርሰውን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ቀሪውን የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት ያካትታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር። |
ያዕቆብ ግን በሰፈሩ አደረ፤ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ማኅደር ብሎ ጠራው።
ዳርቻውም ከሴፋማ በዐይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ አርቤላ ይወርዳል፤ እስከ ኬኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤
ከመካናራ ወሰን ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እርሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረባን፥ ዮርዳኖስንም ሰጠኋቸው።
በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኬኔሬት ባሕር ድረስ፥ በአሴሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፋስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ ሴዎን፤
የጋድ ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም፥ መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። በጠላቶቻቸውም ፊት ጀርባቸውን መልሰው ሸሹ፤ መንደሮቻቸውና ከተሞቻቸው በየወገናቸው ሆነዋልና።