ኢያሱ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች ግን ጌሴሪያውያንን፥ መከጢያውያንንና ከነዓናውያንን አላጠፉአቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴሪና መከጢ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እስራኤላውያን የጌሹርንና የማዕካትን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላቸው ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላስወጡም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እስራኤላውያን የገሹርንና የማዕካን ሕዝብ አላስወጡም፤ ነገር ግን እነርሱ እስከ አሁን በእስራኤላውያን መካከል ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላወጡም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ። |
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።
የሀገሩንም ስዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐናችሁም እንደ አሜከላ ይሆኑባችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤
ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥
በባሳን የነበረውን፥ በአስታሮትና በኤንድራይን የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ከረዓይት የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ አወጣቸው፤ ገደላቸውም።
ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልተሰጠም፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና፥ በኢያሪኮ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች እንዳካፈላቸው እንዲሁ ተካፈሉ።
ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሴራውያንና በአማሌቃውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነዚህንም ቅጽር ባላቸው በጌላምሱርና በአኔቆንጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀምጠው አገኙአቸው።