ኢያሱ 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤላም ንጉሥ፥ የጋዜር ንጉሥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔግሎም ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔግሎን፥ ጌዜር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኦዶላም ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥ የዳቤር ንጉሥ፥ |
እነርሱም ወረሱአት፤ በከነዓን ምድር የሚኖሩትንም ሰዎች በፊታቸው አጠፋሃቸው፤ የሚወድዱትንም ነገር ያደርጉባቸው ዘንድ እነርሱንና ነገሥታቶቻቸውን፥ የምድሩንም አሕዛብ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንንም ንጉሥ፥ የየርሙትንም ንጉሥ፥ የላኪስንም ንጉሥ፥ የአዶላምንም ንጉሥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
በዚያ ጊዜም የጋዜር ንጉሥ ኤላም ላኪስን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር በሰይፍ ስለት እርሱንና ሕዝቡን መታ፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም።