Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚህ ጊዜ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ፤ ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ ንጉሡንና ሕዝቡን መታቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድም እንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚህ ጊዜ የጌዜር ንጉሥ ሆራም ላኪሽን ለመርዳት መጥቶ ነበር፤ ነገር ግን ኢያሱ እርሱንና ሠራዊቱን ድል አደረገ፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድ እንኳ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፥ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:33
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።


ከዚ​ህም በኋላ በጋ​ዜር ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት እንደ ገና ሆነ፤ ያን​ጊ​ዜም ኡሳ​ታ​ዊው ሴቦ​ቃይ ከኀ​ያ​ላን ወገን የነ​በ​ረ​ውን ሲፋ​ይን ገድሎ ጣለው።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ያሉ​ትን የመ​ማ​ፀ​ኛ​ውን ከተ​ሞች ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ደግ​ሞም ጋዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላኪ​ስን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያዙ​አት፤ በል​ብ​ናም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ፥ እር​ስ​ዋን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው።


ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከላ​ኪስ ወደ አዶ​ላም አለፉ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም፤ ወጉ​አ​ትም፤


የኤ​ላም ንጉሥ፥ የጋ​ዜር ንጉሥ፥


በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


ወደ ምዕ​ራ​ብም እስከ የፍ​ሌ​ጣ​ው​ያን ዳርቻ እስከ ታች​ኛው ቤቶ​ሮን ዳርቻ ድረስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።


ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ኤፍ​ሬ​ምም በጋ​ዜር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በጋ​ዜር ተቀ​መጡ፤ ገባ​ሮ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች