የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ር​ስዋ ላይ ሰልፍ አዘ​ጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀ​ት​ርም እን​ውጣ። ቀኑ መሽ​ቶ​አ​ልና፥ የቀ​ኑም ጥላ አል​ፎ​አ​ልና ወዮ​ልን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“በርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤ ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤ ወዮ! ቀኑ እኮ መሸብን! ጥላው ረዘመ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“በእርሷ ላይ ጦርነት አዘጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ።” “ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን!”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጠላቶችዋም እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌምን ለመውጋት እንዘጋጅ! ተነሡ! በእኩለ ቀን ላይ አደጋ እንጣልባት! እንዲያውም ዘግይተናል፤ ቀኑ ሊመሽ ተቃርቦአል፤ ፀሐይም ልትጠልቅ በመቃረብዋ ጥላው እየረዘመ ሄዶአል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 6:4
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?


ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስ​ኪ​ነ​ፍስ፥ ጥላ​ውም እስ​ኪ​ሸሽ ድረስ ተመ​ለስ፤ በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋ​ውን ወይም የዋ​ላ​ውን እን​ቦሳ ምሰል።


መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


ሰባት የወ​ለ​ደች ባዶ ቀረች፤ ነፍ​ስ​ዋም ተጨ​ን​ቃ​ለች፤ በቀ​ትር ጊዜ ፀሐ​ይዋ ገብ​ታ​ባ​ታ​ለች፤ አፍ​ራ​ለች፤ ተዋ​ር​ዳ​ማ​ለች፤ የተ​ረ​ፉ​ት​ንም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ወደ ቅጥ​ርዋ ወጥ​ታ​ችሁ አፍ​ርሱ፤ ነገር ግን ፈጽ​ማ​ችሁ አታ​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸ​ውና መጠ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አት​ርፉ።


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


መከሩ አል​ፎ​አል፤ በጋ​ውም ዐል​ቋል፤ እኛም አል​ዳ​ን​ንም።


“ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፣ አዛጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።