Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ጦረኖች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ይህን ለአሕዛብ ሁሉ ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ጀግኖችን ቀስቅሱ፤ ጦረኞቻችሁ ሁሉ ተሰብስበው ለጦርነት ይሰለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለሰልፍ ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 3:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ወ​ድዱ፥ ክፋ​ትን ጥሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ኑን ነፍ​ሶች ይጠ​ብ​ቃል፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያድ​ና​ቸ​ዋል።


እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።


አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።


በእ​ር​ስዋ ላይ ሰልፍ አዘ​ጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀ​ት​ርም እን​ውጣ። ቀኑ መሽ​ቶ​አ​ልና፥ የቀ​ኑም ጥላ አል​ፎ​አ​ልና ወዮ​ልን።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጎግ እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ደ​ማ​መ​ጣህ፥ በዚ​ያች ዘመን ብዙ ዓመት ትን​ቢት በተ​ና​ገሩ በባ​ሪ​ያ​ዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት እጅ በቀ​ደ​መው ዘመን ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ርሁ አንተ ነህን?


“አን​ተና ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገ​ኖ​ችህ ሁሉ ተዘ​ጋጁ፤ አን​ተም ራስ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተህ ጠባቂ ሁና​ቸው።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።


እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች