የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እንደ አለሌ ፈረ​ሶች ሆኑ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሚስ​ቶች አረ​ከሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጉላ ፈረስ ሆኑ፤ እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደ ተቀለቡ ምኞትም እንዳላቸው ፈረሶች ሆኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ኋላ አሽካኩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደ ተቀለቡ ፈረሶች በፍትወት ስለ ተቃጠሉ፥ እያንዳንዱ ከጓደኛው ሚስት ጋር መዳራት ይፈልጋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደ ተቀለቡ ፈረሶች ሆኑ፥ እያንዳንዳቸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ኋላ አሽካኩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 5:8
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?”


ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ በደ​ጅ​ዋም አድ​ብቼ እንደ ሆነ፥


“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ቤት አት​መኝ፤ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማን​ኛ​ው​ንም አት​መኝ።”


ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም።


አስ​ጸ​ያፊ ሥራ​ሽን፥ ምን​ዝ​ር​ና​ሽን፥ ማሽ​ካ​ካ​ት​ሽን፥ የዝ​ሙ​ት​ሽ​ንም መዳ​ራት በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ፥ በሜ​ዳም ላይ አይ​ቻ​ለሁ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ወዮ​ልሽ! ለመ​ን​ጻት እንቢ ብለ​ሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?


ዝሙ​ታ​ቸው ምድ​ርን ሞል​ት​ዋ​ልና፥ ከመ​ር​ገም ፊት የተ​ነሣ ምድር አል​ቅ​ሳ​ለች፤ የም​ድረ በዳ ማሰ​ሪ​ያው ሁሉ ደር​ቆ​አል፤ ሥራ​ቸ​ውና ድካ​ማ​ቸው ከንቱ ሆነ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሚስ​ቶች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ያላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ቃል በስሜ በሐ​ሰት ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና። እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤


ሁሉም አመ​ን​ዝ​ሮች፥ የዐ​መ​ጸ​ኞች ጉባኤ ናቸ​ውና ሕዝ​ቤን እተ​ዋ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ር​ሱም እለይ ዘንድ በም​ድረ በዳ ማደ​ሪ​ያን ማን በሰ​ጠኝ?


ሰውም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባ​ትም የል​ጁን ሚስት በኀ​ጢ​አት አረ​ከሰ፤ በአ​ን​ቺም ዘንድ ወን​ድም የአ​ባ​ቱን ልጅ እኅ​ቱን አስ​ነ​ወረ።


“ነፍስ አት​ግ​ደል።


“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት አት​መኝ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም ቤት፥ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማና​ቸ​ው​ንም አት​መኝ።