Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት አት​መኝ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም ቤት፥ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማና​ቸ​ው​ንም አት​መኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። በባልንጀራህ ቤትም ሆነ በመሬቱ፣ በወንድ ሆነ በሴት አገልጋዩ፣ በበሬውም ሆነ በአህያው ወይም የርሱ በሆነው በማንኛውም ነገር ላይ ዐይንህን አትጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ ‘የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፥ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም አገልጋዩንና አገልጋይቱን፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ንብረት ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ ‘የሌላውን ሰው ሚስቱን፥ ቤቱን፥ ርስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፤ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 5:21
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ በደ​ጅ​ዋም አድ​ብቼ እንደ ሆነ፥


“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ቤት አት​መኝ፤ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማን​ኛ​ው​ንም አት​መኝ።”


ውበቷ ድል አይንሣህ። በዐይኖችዋ አትጠመድ፥ በቅንድቧም አትማረክ።


በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።


ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት!


“ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።


በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው።


ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች