የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 40:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም እግዚአብሔር አመጣው፤ እንደ ተናገረውም አደረገ። ይህ ሁሉ የሆነው እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና እርሱን ስላልታዘዛችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም አመጣው፥ እንደ ተናገረውም አደረገ፤ በጌታም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ድምፁንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር በእናንተ ላይ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አደርጋለሁ ብሎ ያቀደውን ሁሉ እነሆ አሁን ፈጽሞታል፤ ይህም ሁሉ የሆነው እናንተ ኃጢአት በመሥራታችሁና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ ምክንያት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም አመጣው እንደ ተናገረውም አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ቃሉንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 40:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባረ​ፉም ጊዜ ተመ​ል​ሰው በፊ​ትህ ክፉ አደ​ረጉ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተው​ሃ​ቸው፤ ገዙ​አ​ቸ​ውም፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰ​ማይ ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታደ​ግ​ሃ​ቸው፤


በደ​ረ​ሰ​ብ​ንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ አንተ እው​ነት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ እኛም እጅግ በድ​ለ​ና​ልና።


ለበ​ዓ​ልም በማ​ጠ​ና​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው ስለ ሠሩ​አት ስለ እስ​ራ​ኤ​ልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተ​ከ​ለሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉን ነገር ተና​ግ​ሮ​ብ​ሻል።


ብዙ አሕ​ዛ​ብም በዚች ከተማ ላይ ያል​ፋሉ፤ ሁሉም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ይላሉ።


“ሂድ ለኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊው ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ እን​ዲህ በለው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ለበ​ጎ​ነት ሳይ​ሆን ለክ​ፋት ቃሌን በዚች ከተማ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀን በፊ​ትህ ይፈ​ጸ​ማል።


ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”


ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።


ፌ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በ​ውን አደ​ረገ፤ በቀ​ድሞ ዘመን ያዘ​ዘ​ው​ንም ቃል ፈጸመ፤ አፈ​ረ​ሳት፤ አል​ራ​ራ​ላ​ት​ምም፤ ጠላ​ት​ንም ደስ አሰ​ኘ​ብሽ፤ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደ​ረገ።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


ሰዎ​ችም እን​ዲህ ይላሉ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን ስለ​ተዉ፥