Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ብዙ አሕ​ዛ​ብም በዚች ከተማ ላይ ያል​ፋሉ፤ ሁሉም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ከተለያየ አገር የመጡ ሕዝቦች በዚህች ከተማ በኩል ሲያልፉ፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ለምን እንዲህ አደረገ?’ እያሉ እርስ በርስ ይነጋገራሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ ጌታ በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ?” ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ከዚያን በኋላ በዚያ በኩል የሚያልፉ ብዙ የውጪ አገር ሰዎች ‘በዚህች በታላቅ ከተማ ላይ እግዚአብሔር ይህን ጥፋት ያመጣው ለምን ይሆን?’ በማለት እርስ በርሳቸው ይጠያየቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ? ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 22:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላሜድ። የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ አስ​ጨ​ና​ቂና ጠላት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር እን​ደ​ሚ​ገባ አላ​መ​ኑም።


“ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ።


በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


በሚ​ሄ​ዱ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ መካ​ከል ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይና​ገሩ ዘንድ ከሰ​ይ​ፍና ከራብ፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርም ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችን ከእ​ነ​ርሱ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት እንደ ተማ​ረኩ ያው​ቃሉ፤ ስለ ከዱኝ እኔም ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ ስለ መለ​ስሁ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሰ​ይፍ ወደቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች