Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 40:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነሆ፤ ዛሬ የእጅህን ሰንሰለት ፈታሁልህ። ከፈለግህ ከእኔ ጋራ ወደ ባቢሎን ና፤ እኔም እንከባ ከብሃለሁ፤ ካልፈለግህ ግን አትምጣ። እነሆ፤ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ወደ ቀናህ ሂድ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፥ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፥ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፥ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 40:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።”


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊ​ትህ ናት፤ በወ​ደ​ድ​ኸው ተቀ​መጥ።”


አን​ተም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፦ ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ አልህ።


በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”


ኤር​ም​ያ​ስም፥ “ሐሰት ነው፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን መኰ​ብ​ለሌ አይ​ደ​ለም” አለ፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ውም፤ ሳሩ​ያም ኤር​ም​ያ​ስን ይዞ ወደ አለ​ቆች አመ​ጣው።


ጋሜል። እን​ዳ​ል​ወጣ በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ ሰን​ሰ​ለ​ቴ​ንም አከ​በደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች