Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሮሜ 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ወን​ድ​ሙን ስለ​ሚ​ነ​ቅፍ ሰው

1 አንተ ሰው ሆይ፥ እው​ነት ለሚ​ፈ​ር​ደው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ? በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ጠ​ላ​ውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠ​ራ​ኸው በራ​ስህ የም​ት​ፈ​ርድ አይ​ደ​ለ​ምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠ​ራ​ዋ​ለ​ህና።

2 ይህም እን​ደ​ዚህ በሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርዱ እው​ነት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።

3 አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይ​ተህ የም​ት​ጠ​ላ​ው​ንና የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ውን ያን አንተ ራስህ የም​ት​ሠ​ራው ከሆነ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ ታስ​ባ​ለ​ህን?

4 ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?

5 ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።

6 እርሱ በእ​ው​ነ​ተና ፍርዱ ለሁሉ እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋ​ልና።

7 በበጎ ምግ​ባር ጸን​ተው ለሚ​ታ​ገሡ፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርን፥ የማ​ይ​ጠፋ ሕይ​ወ​ት​ንም ለሚሹ እርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።

8 ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው።

9 መከ​ራና ጭን​ቀት አስ​ቀ​ድሞ በአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም በአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው።

10 ምስ​ጋ​ናና ክብር፥ ሰላ​ምም አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም ለአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ መል​ካም ለሆነ ሁሉ ነው።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና።

12 ከሕግ ወጥ​ተው የበ​ደሉ በሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ያለ ሕግ የበ​ደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል።

13 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።

14 ሕግ የሌ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብስ እንኳ ለራ​ሳ​ቸው ሕግ ይሠ​ራሉ፤ ራሳ​ቸው ለራ​ሳ​ቸው ሕግን ይደ​ነ​ግ​ጋሉ፤ በሕ​ጋ​ቸው የታ​ዘ​ዘ​ው​ንም ያደ​ር​ጋሉ።

15 በል​ባ​ቸው የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕግ ሥራ ያሳ​ያሉ፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ይታ​ወ​ቃል፤ ሕሊ​ና​ቸ​ውም ይመ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ልም።

16 ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እኔ በወ​ን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ ሰዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው የሰ​ወ​ሩ​ት​ንና የሸ​ሸ​ጉ​ትን በሚ​መ​ረ​ም​ር​በት ጊዜ የሚ​ና​ገ​ሩ​ትና የሚ​መ​ል​ሱት እን​ደ​ሌለ ስለ​ሚ​ያ​ውቁ ነው።


ራሱ የማ​ይ​ሠራ ለሌ​ላው የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር

17 አንተ አይ​ሁ​ዳዊ፥ በኦ​ሪ​ትህ የም​ታ​ርፍ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ት​መካ ከሆ​ንህ፥

18 ፈቃ​ዱን የም​ታ​ውቅ፥ መል​ካ​ሙ​ንም የም​ት​ለይ፥ ኦሪ​ት​ንም የተ​ማ​ርህ ከሆ​ንህ፥

19 አንተ የዕ​ው​ሮች መሪ፥ በጨ​ለ​ማም ላሉት ብር​ሃን እንደ ሆንህ በራ​ስህ የም​ት​ታ​መን ከሆ​ንህ፥

20 ሰነ​ፎ​ችን ልባ​ሞች የም​ታ​ደ​ርግ፥ ሕፃ​ና​ትን የም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ጻድ​ቅና የም​ት​ከ​ብ​ር​በ​ትን የኦ​ሪ​ትን ሕግ የም​ታ​ውቅ የም​ት​መ​ስል፥

21 እን​ግ​ዲህ ሌላ​ውን የም​ታ​ስ​ተ​ምር ራስ​ህን እን​ዴት አታ​ስ​ተ​ም​ርም? አት​ስ​ረቁ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰ​ር​ቃ​ለህ።

22 አታ​መ​ን​ዝሩ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለህ፤ ወደ ጐል​ማሳ ሚስ​ትም ትሄ​ዳ​ለህ፤ ጣዖ​ትን ትጸ​የ​ፋ​ለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅ​ደ​ስን ትዘ​ር​ፋ​ለህ።

23 በኦ​ሪት ትመ​ካ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ኦሪ​ትን በመ​ሻር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቃ​ል​ለ​ዋ​ለህ።

24 እንደ ተጻ​ፈም “እነሆ፥ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ይሰ​ድ​ባሉ።”


ስለ ግዝ​ረ​ትና ስለ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት

25 ኦሪ​ት​ንም ብት​ፈ​ጽም ግዝ​ረት ትጠ​ቅ​ም​ሃ​ለች፤ ኦሪ​ትን ባት​ፈ​ጽም ግን ግዝ​ረ​ትህ አለ​መ​ገ​ዘር ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች።

26 አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።

27 ተገ​ዝ​ረህ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ በተ​ፈ​ጥሮ ያገ​ኘ​ሃት አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ አብ​ራህ ብት​ኖር ይሻ​ል​ሃል፤ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ ከአ​ንተ ከተ​ገ​ዘ​ር​ኸው ያ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረው፥ ኦሪ​ትን የሚ​ፈ​ጽ​መው ይሻ​ላል።

28 በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?

29 ዳሩ ግን አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት በስ​ውር ነው፤ መገ​ዘ​ርም በመ​ን​ፈስ የልብ መገ​ዘር እንጂ በኦ​ሪት ሥር​ዐት አይ​ደ​ለም፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ከሰው አይ​ደ​ለም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች