የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁዳ ዘንድ ተና​ገሩ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ አው​ሩና፦ በሀ​ገ​ሪቱ ላይ መለ​ከት ንፉ በሉ፤ ጮኻ​ች​ሁም፦ ሁላ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ወደ ተመ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች እን​ግባ በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤ በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤ ‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ!’

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በይሁዳ ላይ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውጁ፦ “በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ‘ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ’ በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት ንፉ! ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደተመሸጉ ከተሞች እንዲሸሹ ንገሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፥ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 4:5
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”


የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ ለይ​ሁ​ዳም ሰዎች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖሩ ተና​ገሩ፤


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዚች ምድር ላይ በዘ​መተ ጊዜ፦ ኑ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትና ከሶ​ርያ ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሂድ፤ አልን፤ እን​ዲ​ሁም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መ​ጥን።”


ይህ​ንም በያ​ዕ​ቆብ ቤት አውሩ፤ በይ​ሁ​ዳም አሰሙ፦


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?


“መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ ሁሉ​ንም አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን መዓቴ በብ​ዙ​ዎች ሁሉ ላይ ነውና ወደ ሰልፍ የሚ​ሄድ የለም።


በብ​ብ​ታ​ቸው እንደ መሬት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት እንደ ንስር ይመ​ጣል። ቃል ኪዳ​ኔን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ በሕ​ጌም ላይ ዐም​ፀ​ዋ​ልና።


በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በቅ​ዱ​ሱም ተራ​ራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይደ​ን​ግጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን መጥ​ቶ​አ​ልና፥ እር​ሱም ቀር​ቦ​አ​ልና።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


አን​በ​ሳው አገሣ፤ የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፤ ትን​ቢት የማ​ይ​ና​ገር ማን ነው?


“ሁለት የብር መለ​ከ​ቶች አስ​ጠ​ፍ​ጥ​ፈህ ለአ​ንተ አድ​ርግ፤ ማኅ​በ​ሩን ለመ​ጥ​ራት ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም ለማ​ስ​ጓዝ ይሁ​ኑ​ልህ።


ሁለ​ቱም መለ​ከ​ቶች በተ​ነፉ ጊዜ ማኅ​በሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይሰ​ብ​ሰቡ።


እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥