Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከሰ​ሜን ክፉ ነገ​ር​ንና ጽኑ ጥፋ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና ዓላ​ማ​ች​ሁን አንሡ፤ ወደ ጽዮ​ንም ሽሹ፥ ፍጠኑ፥ አት​ዘ​ግዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ ከሰሜን መቅሠፍትን፣ ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለጽዮን መንገዱን አመልክቱአት! ሳትዘገዩ የደኅንነት ዋስትና ወደሚገኝበት ስፍራ ሽሹ! እግዚአብሔር ከሰሜን በኩል መቅሠፍትና ታላቅ ጥፋት ሊያመጣ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፥ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:6
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕ​ዝ​ቤም መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ከጎ​ዳ​ናው አስ​ወ​ግዱ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አላማ ያዙ።


የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነ​ሆም የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ባድ​ማና የሰ​ገኖ ማደ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ከሰ​ሜን ምድር ታላቅ መነ​ዋ​ወጥ መጥ​ቶ​አል።


አሁን እን​ግ​ዲህ ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈ​ጥ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ምክ​ር​ንም እመ​ክ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ሁላ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁ​ንም አቅኑ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው።”


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


የሚ​አ​ጠ​ፋ​ህን ሰው በአ​ንተ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ዛፍ​ህ​ንም በም​ሳር ይቈ​ር​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላል።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የሚ​ሸ​ሹ​ትን የም​መ​ለ​ከት፥ የመ​ለ​ከ​ቱ​ንስ ድምፅ የም​ሰማ እስከ መቼ ነው?


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


የሰ​ል​ፍና የታ​ላቅ ጥፋት ውካታ በም​ድር ላይ አለ።


በባ​ቢ​ሎን ቅጥ​ሮች ላይ ዓላ​ማ​ውን አንሡ፤ ከጕ​ራ​ን​ጕ​ሬ​አ​ችሁ ጋር ጽኑ፤ ተመ​ል​ካ​ቾ​ችን አቁሙ፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖ​ሩት ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።


“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።


“ከባ​ቢ​ሎን የጩ​ኸት ድምፅ፥ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር የታ​ላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።


እር​ሱም፥ “እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ባት መሣ​ሪ​ያን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ቀ​ሥፉ ይቅ​ረቡ” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ በጆ​ሮዬ ጮኸ።


እነ​ሆም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ገጀሞ መሣ​ሪያ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ስድ​ስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚ​መ​ለ​ከ​ተው ከላ​ይ​ኛው በር መን​ገድ መጡ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የበ​ፍታ ልብስ የለ​በ​ሰና የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂያ በወ​ገቡ የታ​ጠቀ አንድ ሰው ነበረ። እነ​ር​ሱም ገብ​ተው በናሱ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ቆሙ።


በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከዓሣው በር የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ውካታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።


ዱሪ ፈረሶች ያሉበት ወደ ሰሜን ይወጣል፣ አምባላዮቹም ከእነርሱ በኋላ ይወጣሉ፥ ቅጥልጣሎቹም ወደ ደቡብ ይወጣሉ አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች