የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በብ​ርና በወ​ርቅ ይለ​ብ​ጡ​ታል፤ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም በች​ን​ካ​ርና በመ​ዶሻ ይቸ​ነ​ክ​ሩ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤ እንዳይወድቅም፣ በመዶሻ መትተው በምስማር ያጣብቁታል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤ እንዳይወድቅም በምስማር ያጠብቁታል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 10:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሕ​ይ​ወ​ትን ጽዋ እቀ​በ​ላ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።


ፈር​ዖ​ን​ንና ሠራ​ዊ​ቱን በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ብረት ሠሪ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ውን ይስ​ላል፤ ጣዖ​ቱን በመ​ጥ​ረ​ቢያ ይቀ​ር​ጸ​ዋል፤ በመ​ዶ​ሻም መትቶ ቅርጽ ይሰ​ጠ​ዋል፤ በክ​ን​ዱም ኀይል ይሠ​ራ​ዋል፤ እር​ሱም ይራ​ባል፤ ይደ​ክ​ም​ማል፤ ውኃም አይ​ጠ​ጣም።


ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


ዳግ​መ​ኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚ​ሠ​ራው አም​ሳል ከወ​ር​ቃ​ቸ​ውና ከብ​ራ​ቸው ጣዖ​ትን ሠሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አል​ቋል።”


እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።